በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት መካከል የነበረውን ግንኙነት ማደስ በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ውይይት ተደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት መካከል የነበረውን ግንኙነት ማደስ በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ውይይት ተደረገ
አዲስ አበባ ሰኔ 27/2015(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት መካከል የነበረውን ግንኙነት ማደስ በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ውይይት ተደረገ።
በቤልጅየም፣ ሉክዘምበርግ ኔዘርላንድ እና በአውሮፓ ህብረት ተቋማት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከአውሮፓ ህብረት የውጭ ተግባር አገልግሎት ምክትል ዋና ጸሓፊ ኤነሪኬ ሞራ ጋር በኢትዮጵያና በአውሮፓ ህብረት መካከል የነበረውን ግንኙነት ማደስ በሚቻልበት ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም የጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን በብራሰልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።