ቀጥታ፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ ሰኔ 27/2015 (ኢዜአ)፦ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል፡፡

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መዋቅር ስር  የነበሩ የስድስት ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ሕዝቦች ያካሄዱትን ሕዝበ ውሳኔ አስመልክቶ የሚያቀርበውን ሪፖርት ያዳምጣል፡፡

ሕዝበ ውሳኔውን አስመልክቶም በቋሚ ኮሚቴው የሚቀርበውን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ሌሎች መደበኛ የመወያያ አጀንዳዎችን በማጽደቅ እየተወያየ እንደሚገኝም በመረጃው ተመላክቷል፡፡

ምክር ቤቱ ያጸደቃቸውን አጀንዳዎች በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ  እንደሚጠበቅም በመረጃው ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም