ቀጥታ፡

የሲዳማ ክልል ሶስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል እየተከበረ ነው

ሀዋሳ ሰኔ 27/2015(ኢዜአ)፦ የሲዳማ ክልል ሶስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።

በበዓሉ ላይ በክልል ከተደራጀ በኋላ በተለያዩ ዘርፎች የተገኙ ትሩፋቶች የሚዘክር ጽሑፍ እንደመቀርብ ይጠበቃል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ፣ የብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እንዲሁም የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በአካባበር ሥነ-ሥርዓት ላይ ታድመዋል።

የሲዳማ ክልል የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 10ኛ ክልል ሆኖ የተመሰረተው ሰኔ /2012 ዓ.ም እንደሆነ ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም