ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን እና የቻይናው ዙምሊዮን ኩባንያ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ሰኔ 27/2015(ኢዜአ):-የኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን እና የቻይናው ግዙፍ ኩባንያ ዙምሊዮን በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።

ሶስተኛው የቻይና-አፍሪካ የኢኮኖሚ እና የንግድ አውደ ርዕይ በቻይና ሁናን ግዛት ቻንግሻ ከተማ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል።

አውድ ርዕዩ “የጋራ ልማት ለጋራ ራዕይ” በሚል መሪ ሀሳብ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን የአፍሪካ የወይን፣ ቡና፣በእጅ የተሰሩ የዕደ ጥበብ ስራዎች እና የተለያዩ ምርቶች እንዲሁም የቻይና የምህንድስና ማሽኖች፣የሕክምና መሳሪያዎች፣የንግድ ምርቶች እና የግብርና መሳሪዎች ቀርበዋል።

በአውደ ርዕዩ ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ከቻይናው ግዙፍ የግብርና እና ኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች አምራች ኩባንያ ዙምሊዮን ጋር በግብርና ማሽነሪዎች ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈራርሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም