የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በጅዳ የኢትዮዽያ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት እየተሰጠ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በጅዳ የኢትዮዽያ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት እየተሰጠ ነው
አዲስ አበባ ሰኔ 26/2015 (ኢዜአ) ፦ የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከዛሬ ጀምሮ በጅዳ የኢትዮዽያ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት መሰጠት መጀመሩ ተገለጸ።
የፈተናውን ስነ-ሥርዓት ከአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ፣ በጅዳ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ተወካዮችና የትምህርት ቤቱ የአመራር አካላት ተገኝተው ማስጀመራቸው ተመላክቷል።
በዛሬው እለትም የፈተናው ሂደት በሰላም ሲከናወን መዋሉንና ነገ የሚጠናቀቅ መሆኑን በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።