ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን /ኢቢሲ/  "በዘመን ጅረት" በሚል ያዘጋጀውን የፎቶ ግራፍ አውደ  ርዕይ ተከፈተ 

አዲስ አበባ ሰኔ 26/2015(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን /ኢቢሲ/ አዲስ ባስገነባው የሚዲያ ኮምፕሌክስ "በዘመን ጅረት" በሚል ያዘጋጀውን የፎቶ ግራፍ አውደ- ርዕይ  ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ከፍተውታል።

አውደ- ርዕዩ ኢቢሲ በቴሌቭዥንና በሬዲዮ ቴክኖሎጂ ያለፈባቸውንና አሁን ያለበትን የስራ ዕንቅስቃሴ የሚያሳይ ነው።

አፈ- ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ከተለያዩ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን የስራ ሀላፊዎች ጋር በመሆን አውደ-ርዕዩን ጎብኝተውታል።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤን ጨምሮ የኦቢኤን፣ ዋልታና ሌሎች የሚዲያ ከፍተኛ ሀላፊዎች በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እያስገነባ ያለውን  የሚዲያ ኮምፕሌክስ 5 የቲቪና  3 የሬዲዮ እስቲዲዮ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳና ሌሎች አገልግሎት የሚሰጡ ቦታዎችን በውስጡ ይዟል።

የኢቢሲ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ግንባታው ከአንድ አመት በፊት የተጀመረ ሲሆን ከነገ ወዲያ ረቡዕ  ይመረቃል ተብሏል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም