በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ፈተና በመሰጠት ላይ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ፈተና በመሰጠት ላይ ነው
አዲስ አበባ ሰኔ 26/2015(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ዛሬ ማለዳ መሰጠት ተጀምሯል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ቅኝት ባደረገባቸው በየካ ክፍለ ከተማ ሚያዚያ 23 ትምህርት ቤትና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ገሊላ ትምህርት ቤት ፈተናው በሰላማዊ መንገድ መሰጠት መጀመሩን አረጋግጧል።
ሚያዚያ 23 ትምህርት ቤት 576 የቀንና የማታ ተማሪዎች ለፈተና ተቀምጠዋል።
በትምህርት ቤቱ በፈተና ወቅት ለሚያጋጥሙ የጤናም ሆነ ሌሎች ችግሮች ቅድመ ዝግጅት ማድረጉም ተገልጿል።
ፈተናው በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ የከተማው ትምህርት ቢሮ ከፈተና ዝግጅት አንስቶ የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ እሰከሚጠናቀቅ ኮማንድ ፖስት አቋቁሞ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በመዲናዋ 75 ሺህ 100 የ8ኛ ክፍል ተፈታኞች በ182 የመፈተኛ ጣቢያ እየተፈተኑ ነው፡፡
ዛሬ መሰጠት የተጀመረው ፈተና ነገ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡