ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሕብረት ስራ ማሕበራት የተደራጁ የጋራ የመኖሪያ ቤት ቆጣቢዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የቤት ግንባታ አስጀመሩ - ኢዜአ አማርኛ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሕብረት ስራ ማሕበራት የተደራጁ የጋራ የመኖሪያ ቤት ቆጣቢዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የቤት ግንባታ አስጀመሩ
አዲስ አበባ ሰኔ 26/2015(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ54 የመኖሪያ ሕብረት ስራ ማሕበራት ለተደራጁ 4 ሺህ በላይ የጋራ የመኖሪያ ቤት ቆጣቢዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የቤት ግንባታን ዛሬ አስጀምረዋል።
ከንቲባ አዳነች የከተማ አስተዳደሩ “የነዋሪው ቀዳሚ ጥያቄ የሆነውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ አዳዲስ አማራጭ አሰራሮችን እና ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል” ብለዋል።
የጋራ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ቆጣቢ የከተማው ነዋሪዎች አስተዳደሩ ያዘጋጀውን አማራጭ ተጠቅመው በማህበር በመደራጀት እና በመቆጠብ የቤት ባለቤት መሆን እንደሚችሉ አመልክተዋል።
በግንባታው የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ስነ- ስርዓት ላይ ከንቲባዋን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል።