ቀጥታ፡

በፕሪሚየር ሊጉ ባህር ዳር ከተማ ሃዋሳ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ ሰኔ 25/2015 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማምሻውን በአዳማ ሳይስን እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ የ29ኛ ሳምንት ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ ሃዋሳ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

የአማካይ ተጫዋቹ ያብስራ ተስፋዬ የመጀመሪያ አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በጭማሪ ሰአት ለጣና ሞገዶቹ የማሸነፊያዋን ግብ አስቆጥሯል።

ውጤቱንም ተከትሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ባህር ዳር ከተማ ነጥቡን ወደ 57 ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ ሃዋሳ ከተማ በ41 ነጥብ በነበረበት 6ኛ ደረጃ ላይ ረግቷል።

ቀን ላይ በተካሄደው የ29ኛ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዲያ ሆሳናን 2 ለ 0 በማሸነፍ የሊጉን ዋንጫ ለ16ኛ ጊዜ ማንሳቱን ማረጋገጡ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም