በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2015 ሻምፒዮን ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2015 ሻምፒዮን ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25/2015(ኢዜአ)፦ ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ጨዋታ እየቀረው የ2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋገጠ፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን የ2015 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን የሆነው ሀድያ ሆሳዕናን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሀድያ ሆሳዕና ያገናኘው የ29ኛ ሳምንት ጨዋታ 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ጨዋታ እየቀረው ሻምፒዮን የሆነባቸውን ግቦች ቸርነት ጉግሳ እና እስማኤል ኦሮ አጎሮ አስቆጥረዋል፡፡