ቀጥታ፡

የላቀች ኢትዮጵያን ለመገንባት፤ ቀድመን የላቁ ትምህርት ቤቶችን አብረን እንገንባ-ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ

አዲስ አበባ ሰኔ 25/2015(ኢዜአ)፦ "የላቀች ኢትዮጵያን ለመገንባት፤ ቀድመን የላቁ ትምህርት ቤቶችን አብረን እንገንባ" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በየትኛውም የኢትዮጵያ ጫፍ የተማራችሁ ሁሉ ትናንት የተማራችሁባቸው ትምህርት ቤቶች ዛሬ የናንተን ድጋፍ ይሻሉ ብለዋል።

ድጋፋችንን በተግባር ለማሳየት ሁላችንም በሐሳብ፣ በገንዘብ፣ በጉልበት እንዲሁም ያለንን ሁሉ ለትምህርት ቤቶች ለማዋል የሚያስችለንን "ትምህርት ለትውልድ" ሀገራዊ ንቅናቄ አስጀምረናል ሲሉም አክለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ባሰፈሩት መልዕክትም የላቀች ኢትዮጵያን ለመገንባት፤ ቀድመን የላቁ ትምህርት ቤቶችን አብረን እንገንባ በማለት ጥሪ አቅርበዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም