ቀጥታ፡

የግብርና እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሮች በቻይና-አፍሪካ የንግድና ኢኮኖሚ ኤክስፖ ላይ እየተሳተፉ ነው


አዲስ አበባ ሰኔ 23/2015(ኢዜአ)፦ የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በቻይና ሁናን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የቻይና አፍሪካ የንግድና ኢኮኖሚ ኤክስፖ 2023 ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።


 

ዶክተር ግርማ አመንቴ የኤክስፖው አካል በሆነው “የቻይና-አፍሪካ ሳኒቴሽንና ፊቶ ሳኒቴሽን ትብብር” በተሰኘ መድረክ ላይ በመሳተፍ ንግግር ማድረጋቸውን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬም እንዲሁ በቻይና ሁናን ከተማ “ማህበራዊ ሃላፊነትና የቻይና አፍሪካ ትብብር” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው 3ኛው የቻይና አፍሪካ የኢኮኖሚና ንግድ ኤክስፖ 2023 ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም