የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም አስፈፃሚ ተቋማት ፕሮጀክቶቻቸውን በከፍተኛ ኃላፊነት እና ፍጥነት ማጠናቀቅ አለባቸው-የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም አስፈፃሚ ተቋማት ፕሮጀክቶቻቸውን በከፍተኛ ኃላፊነት እና ፍጥነት ማጠናቀቅ አለባቸው-የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ
አዲስ አበባ ሰኔ 23/2015(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም አስፈፃሚ ተቋማት ፕሮጀክቶቻቸውን በከፍተኛ ኃላፊነት እና ፍጥነት መስራትና ማጠናቀቅ እንዳለባቸው የአብይ ኮሚቴው ሰብሳቢ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ አሳሰቡ።
የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ብሄራዊ ኮሚቴ የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም የ2015 አፈፃፀም እና የ 2016 እቅድ ገምግሟል።
በግምገማው በፕሮግራሙ ስር ያሉ ስራዎች በተለያዩ ምክንያቶች መጓተት እንደታየባቸው መገምገሙን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም አስፈፃሚ ተቋማት ፕሮጀክቶቻቸውን በከፍተኛ ኃላፊነት እና ፍጥነት መስራትና ማጠናቀቅ እንደሚገባቸውም ነው የአብይ ኮሚቴው ሰብሳቢና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ያሳሰቡት።
ፕሮጀክቱ ለመጠናቀቅ 3 አመታት ብቻ እንደሚቀረው ገልጸው የፕሮጀክት ተጠቃሚ ተቋማት በቅንጅትና በትብብር መስራት አለባቸው ብለዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ሚኒስቴር፣ የኮሙኒኬሽን ባለስልጣንና ብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም አስፈፃሚ ተቋማት መሆናቸውም ተገልጿል።