ቀጥታ፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታቸው ለተረጋገጠላቸው 3 ሺህ 451 አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ሰጠ


አዲስ አበባ ሰኔ 23/2015(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታቸው ለተረጋገጠላቸው 3 ሺህ 451 አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ሰጠ።

የይዞታ ማረጋገጫ ካርታውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ቡዜና አልቃድርና ሌሎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች አስረክበዋል።

የይዞታ ማረጋገጫ ርክክብ ስነ-ስርአቱ የከተማዋ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እና ይዞታቸው የተረጋገጠላቸው አርሶ አደሮች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።


 

የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የተሰጠው በቦሌ፣ በየካ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በለሚ ኩራና በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተሞች ለሚኖሩ አርሶ አደሮች መሆኑ ተገልጿል።

የይዞታ ማረጋገጫ መሰጠቱ አርሶ አደሩ መሬቱን በደላሎች እንዳይነጠቅ፣ ህገ-ወጥነትን ለመከላከል፣ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ፣ የአርሶ አደሩን መብት ለማስከበር ያስችላል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም