የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ከአዲሱ የኤፍ.ቢ.አይ ሌጋል አታሼ ሚስተር ዴኒስ ዌብስተር ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ከአዲሱ የኤፍ.ቢ.አይ ሌጋል አታሼ ሚስተር ዴኒስ ዌብስተር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ከአዲሱ የኤፍ.ቢ.አይ ሌጋል አታሼ ሚስተር ዴኒስ ዌብስተር ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ የተካሄደው በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዋናው መሥሪያ ቤት መሆኑንም ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።
በውይይቱ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፤ የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ህብረት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ መሳተፋቸውም ተገልጿል።
ውይይቱ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በተለይም ሽብርተኝነትን መከላከል ላይ ያተኮረ እንደነበርም በመረጃው ተመላክቷል።
በተጨማሪም ኤፍ.ቢ.አይ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጋር ያለውን ግንኙነት በተለያዩ ድጋፎች ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡