ቀጥታ፡

1 ሺህ 444ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በተለያዩ ከተሞች እየተከበረ ነው

ቦንጋ ሰኔ 21/2015(ኢዜአ)፦ 1 ሺህ 444ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የተለያዩ ከተሞች በመከበር ላይ ይገኛል።

በዓሉ በቦንጋ እንዲሁም በሚዛን አማን ከተማ yአደባባይ ሶላትን ጨምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ- ስርዓቶች እየተከበረ ነው።

በሚዛን ከተማ እየተካሄደ ባለው የበዓሉ ስነ-ስርዓት ላይ የከተማው ከንቲባ አቶ ግሩም ተማም የእምነቱ ተከታዮች እና ሌሎች የመንግስት አመራሮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም