1ሺህ 444ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሃዋሳ፣ ጅንካ እና አርባ ምንጭ ከተሞች እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
1ሺህ 444ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሃዋሳ፣ ጅንካ እና አርባ ምንጭ ከተሞች እየተከበረ ነው
ሃዋሳ፣ ጅንካ፣ አርባ ምንጭ ሰኔ 21/2015(ኢዜአ)፦ 1 ሺህ 444ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሃዋሳ፣ ጅንካ እና አርባ ምንጭ ከተሞች እየተከበረ ይገኛል።
በሀዋሳ ከተማ ሚሊኒየም አደባባይ በዓሉን አስመልክቶ የኢድ ሶላት ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው።
በተመሳሳይ የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በጅንካ ከተማ በቀድሞ አየር ማረፊያ እንዲሁም በአርባ ምንጭ ከተማ ተክቢራ እና ሶላትን ጨምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ነው።