ቀጥታ፡

በኢጋድ ዋና ፀሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ቤልጂየም ገባ 


አዲስ አበባ ሰኔ 20/2015(ኢዜአ)፦ በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የተመራ ልዑካን ቡድኑ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ቤልጂየም ገብቷል።

ልዑካን ቡድኑ ዛቬንተም ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በአውሮፓ ሕብረት የሚገኙ የኢጋድ አባል አገራት አምባሳደሮች አቀባበል አድርገውለታል።


 

የጉብኝቱ ዓላማ የኢጋድ እና የአውሮፓ ሕብረትን ትብብር ማጠናከር መሆኑ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም