የኢትዮጵያ ባህር ኃይል በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን ባህረኞች አስመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ባህር ኃይል በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን ባህረኞች አስመረቀ
አዲስ አበባ ሰኔ 20/2015 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን ባህረኞች አስመረቀ፡፡
ተመራቂዎቹ በናቪጌሽን፣ በኢንጂነሪንግ፣ ኤሌክትሪሲቲ፣ በኮሙኒኬሽን እና በአርማመንት ሙያ በሀገር ውስጥና በውጭ የሰለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል።
በምርቃ መርሐ ግብሩ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ዋና አዛዥ ሪር አድሚራል ክንዱ ገዙ፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች፣ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ጠንካራና ብቃት ያለው በየትኛውም የውሃ አካል ላይ ግዳጅን መወጣት የሚችልና የመከላከያ ኃይል ላይ ተጨማሪ የማድረግ አቅምን የሚፈጥር ተቋም የመሆን ራዕይ ይዞ እየሠራ መሆኑ ተገልጿል።
በኢትዮጵያ እና በብሔራዊ ጥቅሞቿ ላይ በአካባቢው ከሚገኙ የውሃ አካላት ሊሰነዘር የሚችል ጥቃትን የመከላከልና የመመከት ተልዕኮውን ለማሳካትም በሰው ኃይል ልማት ላይ በስፋት እየሠራ ስለመሆኑም ተመላክቷል።