ቀጥታ፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጥገና የተደረገላቸው ፈጣን ተዋጊ ጀልባዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ ሰኔ 20/2015 (ኢዜአ) ፦ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የአየር ኃይል አቪዬሽን ከባድ ጥገና ማዕከል ወደ አገልግሎት የመለሳቸውን ፈጣን ተዋጊ ጀልባዎችን ጎበኙ።

ተዋጊ ጀልባዎቹ በቀድሞ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አገልግሎት የሠጡ ሲሆን ዳግም የባሕር ኃይሉን ዝግጁነት እንደሚያጠናክሩ ተገልጿል።

የኢፌዴሪ አየር ኃይል አቪዬሽን ከባድ ጥገና ማዕከል ከ30 አመት በላይ ተገለው እና አገልግሎት መስጠት ያቆሙ ጀልባዎችን ዘመኑ የሚጠይቀውን የፈጣን ተዋጊ ጀልባ ቴክኖሎጂ እና መሳሪያዎች በመግጠም ለግዳጅ ዝግጁ ማድረግ መቻሉን የመከላከያ ሠራዊት በማህበራዊ ትስስር ገፁ ያሰፈረው መረጃ ያመለክታል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከጉብኝታቸው በኋላ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ያሰለጠናቸውን መሠረታዊ ባሕረኞች ያስመርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም