የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሀዋሳ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሀዋሳ ገቡ
ሐዋሳ ሰኔ 17/2015 (ኢዜአ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሀዋሳ ገቡ።
ፕሬዚዳንቷ ሀዋሳ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞና በክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በሀዋሳ "አሞራ ገደል" እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በተዘጋጀ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አረንጓዴ አሻራቸውን እንደሚያኖሩ ታውቋል።
ከችግኝ ተከላው በተጨማሪ በሲዳማ ክልል ሞዴል የሌማት ትሩፋት የዶሮ እርባታ መንደርን ይመርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በመርሀግብሩ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ሚኒስትሮችና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች እንደሚገኙ ታውቋል።