የአየር ንብረት ለውጥ እና አረንጓዴ አሻራ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የአየር ንብረት ለውጥ እና አረንጓዴ አሻራ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ሰኔ 16/2015(ኢዜአ)፡- የአየር ንብረት ለውጥ እና አረንጓዴ አሻራ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ውይይቱ እየተከናወነ የሚገኘው “የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖዎችን በአረንጓዴ አሻራ መዋጋት” በሚል መሪ ሀሳብ ነው።
ውይይቱን ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢኒስቲትዩት በጋራ በመተባበር ነው።
በውይይቱ መክፈቻ ላይ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም፣ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የቦርድ አባል እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፣ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሴ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ተቋማት እና ምሁራን፣ የዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በውይይቱ ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ በመነሳት የአየር ንብረት ለውጥ እያሳደረ ያለውን ተጽእኖ ላይ የመፍትሔ ሀሳቦች እንደሚመላከቱበት ተገልጿል።
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ተሞክሮ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ለቀጣናዊ ሰላም እና ደህንነት እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ከባለድርሻ አካላት ባሻገር የማህበረሰቡና የመገናኛ ብዙሃን ሚናን የተመለከቱ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ተጠቁሟል።