ቀጥታ፡

ዲጂታል ዲፕሎማሲ በዓለም አቀፍ ግንኙነት ውስጥ ቁልፍ የዲፕሎማሲ አቅም መፍጠሪያ ሆኗል-ኢጋድ 


አዲስ አበባ ሰኔ 15/2015(ኢዜአ)፡- “ዲጂታል ዲፕሎማሲ በዓለም አቀፍ ግንኙነት ውስጥ ቁልፍ የዲፕሎማሲ አቅም መፍጠሪያ ሆኗል” ሲል የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት(ኢጋድ) አስታወቀ።

ዲጂታላይዜሽን የመንግስታትን የእርስ በእርስ ግንኙነት ወደ ተሻለ ምዕራፍ ማሳደጉም ገልጿል።
የኢጋድ ቀጣናዊ የዲጂታል ዲፕሎማሲ ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል። 


 

ጉባኤው የኢጋድ አባል አገራት በዲጂታል ዲፕሎማሲ የእውቀት፣ ልምድ እና ሀሳብ ልውውጥ እንዲያደርጉ ማስቻል መሆኑ ተገልጿል።

የኢጋድ የውጭ አገልግሎት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር መሐመድ ኦማር ጃማ “የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዲጂታል ዲፕሎማሲ በዘመናዊ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ውስጥ ቁልፍ የአቅም መፍጠሪያ መሳሪያዎች አንዱ መሆኑን አሳይቷል” ብለዋል።

የኢጋድ ቀጣናዊ የዲጂታል ዲፕሎማሲ ጉባኤ እስከ ነገ የሚቆይ ሲሆን ጉዳዩን የተመለከቱ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም