የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለት ረቂቅ ደንቦችን ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መራ - ኢዜአ አማርኛ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለት ረቂቅ ደንቦችን ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መራ
አዲስ አበባ ሰኔ 15/2015(ኢዜአ)፡- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የቀረበውን እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የሰራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንቦችን ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል።
ምክር ቤቱ ዛሬ 25ኛ መደበኛ ስብሰባውን አድርጓል።
ምክር ቤቱ በስብሰባው የፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የሰራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንቦች ላይ ተወያይቷል።
በረቂቅ ደንቦቹ ላይ የምክር ቤቱ አባላት አስተያየት እና ጥያቄዎችን አንስተዋል።
ምክር ቤቱ ረቂቅ ደንቦቹን መርምሮ የፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የተዘጋጀውን ረቂቅ ደንብ ለሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የሰራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንብን ለዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።