ቀጥታ፡

በአፍሪካ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ላይ የሚያተኩር ስብሰባ በአዲሰ አበባ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ሰኔ 15/2015(ኢዜአ)፡- የአፍሪካ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን በእኩልነትና በምክንያታዊነት መጠቀም የሚያስችል ሁለተኛው ከፍተኛ የሚኒስትሮች ስብሰባ ዛሬ እና ነገ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

ስብሰባው “የእኩል ምክንያታዊ የድንበር ተፋሰስ ወንዞች ተጠቃሚነት ለአፍሪካ ብልፅግና ወሳኝ” ነው በሚል መሪ ሃሳብ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የስብስባው ዋና አላማ ድንበር ተሻጋሪ ውሃ ለማልማት ምክንያታዊ እና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ የውሃ ሀብትን አጠቃቀም ፅንሰ ሀሳብ ውስጥ የናይል ወንዝን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ የመጠቀም ጉዳይን እንዴት እውን ማድረግ ይቻላል? በሚለው ሀሳብ ላይ መምከር መሆኑ ተመላክቷል።

ለዚህም ፍትሐዊ የውሃ ሀብት አጠቀቃምን በተቀመጡ አሰራሮች እና አማራጮች እንዲሁም ሳይንሳዊ የጥናት ውጤቶች ላይ እንዲመረኮዝ የማድረግ አስፈላጊነትም ውይይት እንደሚደረግበት ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።

በመድረኩም ከናይል ተፋሰስ የተውጣጡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሚሳተፉ ሲሆን የታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም