ቀጥታ፡

የአፍሪካ የሕዝብ አገልግሎት ቀን እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ሰኔ 14/2015(ኢዜአ):-ዘጠነኛው የአፍሪካ የሕዝብ አገልግሎት ቀን ዛሬ በዚምባቡዌ መከበር ጀምሯል።

ቀኑ እየተከበረ የሚገኘው “ለአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስኬታማነት ብቁ የሆነ አህጉራዊ የሕዝብ አስተዳደር ያስፈልጋል” በሚል መሪ ሀሳብ ነው።

ለሶስት ቀናት የሚቆየው አከባበር የተዘጋጀው በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የፖለቲካ ጉዳዮች፣የሰላም እና ደህነነት የስራ ክፍል እና በዚምባቡዌ መንግስት ትብብር መሆኑ ተገልጿል።

የአፍሪካ የሕዝብ አገልግሎት ቀን ሀሳብ የተጠነሰሰው እ.አ.አ በ1994 በሞሮኮ ታንጂየር ከተማ የሕዝብ አገልግሎት ሚኒስትሮች ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረጉት ፓን አፍሪካዊ ስብስባ ላይ ነው።

በስብሰባው ቀኑ በየዓመቱ እ.አ.አ ሰኔ 23 እንዲከበር የተወሰነ ሲሆን አላማውም ለማህበረሰብ አገልግሎቶች ክብር እና እውቅና መስጠት እንደሆነ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም