በእንግሊዝ መንግስት በማደግ ላይ ያሉ አገራትን የውጭ ንግድ ለማሻሻል የሚረዳ የንግድ ፕሮግራም ይፋ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
በእንግሊዝ መንግስት በማደግ ላይ ያሉ አገራትን የውጭ ንግድ ለማሻሻል የሚረዳ የንግድ ፕሮግራም ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ ሰኔ 12/2015(ኢዜአ):- በእንግሊዝ መንግስት አማካኝነት በማደግ ላይ ያሉ አገራትን የውጭ ንግድ ለማሻሻል የሚረዳ የንግድ ፕሮግራም( A Developing Countries trading scheme (DCTS) ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ ሆኗል።
በፕሮግራሙ መክፈቻ ስነ-ስርዓት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ ፣ የእንግሊዝ የዓለም አቀፍ ንግድ ሚኒስትር ናይጅል ሁድልስተን፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሐመድ እና ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በንግድ ፕሮግራሙ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንደምትሆን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል።
ፕሮግራሙ ጠንካራ የኢኮኖሚ እና የንግድ ግንኙነት እንዲፈጠር ከማገዙ ባሻገር የስራ ዕድልን በመፍጠር የወጪ ንግድን በመጨመር፣ ታሪፍን በመቀነስ እንዲሁም የንግድ ቅድመ ሁኔታዎችን በማቅለል ለኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ማደግ ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው ተገልጿል።