ቀጥታ፡

የባለአነስተኛ ይዞታ አርሶ አደሮችን ይበልጥ ምርታማና ተጠቃሚ ለማድረግ በቂ የግብርና ፋይናንስ አገልግሎት ማቅረብ ያስፈልጋል-ዶክተር ግርማ አመንቴ

አዲስ አበባ ሰኔ 12/2015(ኢዜአ)፦ የባለአነስተኛ ይዞታ አርሶ አደሮችን ይበልጥ ምርታማ እና ከምርታቸው ተጠቃሚ ለማድረግ በቂና የተቀላጠፈ የግብርና ፋይናንስ አገልግሎት ማቅረብ ያስፈልጋል ሲሉ የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ ተናገሩ።

ባለድርሻ አካላትን ያካተተ የፋይናንስ አገልግሎት እና በዘርፉ ባሉ እድሎችና ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ ብሄራዊ የግብርና ፋይናንስ አገልግሎት ምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡


 

በዚህ ወቅት ንግግር ያደረጉት የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ በአስር ዓመቱ የግብርና መሪ ዕቅድ ውስጥ ልዩ ትኩረት የሚሹ ተብለው ከተለዩ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው ለግብርና ዘርፍ የፋይናንስ ተደራሽነትን ማስፋት ነው ብለዋል።

በመሆኑም የባለአነስተኛ ይዞታ አርሶ አደሮችን ይበልጥ ምርታማ እና ከምርታቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ በቂና የተቀላጠፈ የግብርና ፋይናንስ አገልግሎት ማቅረብ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

የግብርና የፋይናንስ አገልግሎት እና ተደራሽነት ላይ ይበልጥ ውጤታማ መሆን የሚቻለው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ትኩረት እና ድጋፍ ሲሰጡ መሆኑን ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም በአስር ዓመቱ የግብርና መሪ ዕቅድ ውስጥ ልዩ ትኩረት የሚሹ ተብለው ከተለዩ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው ለግብርና ዘርፍ የፋይናንስ ተደራሽነትን ማስፋት እንደሆነ ገልፀዋል።

በዚህም በአገራችን ግብርና ውስጥ ጉልህ ድርሻ የያዙትን የባለአነስተኛ ይዞታ አርሶ አደሮችን ይበልጥ ምርታማ እና ከምርታቸውም ተጠቃሚ እንዲሆኑ በቂ የሆነና የተቀላጠፈ የግብርና የፋይናንስ አገልግሎት ማቅረብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡


 

የብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለግብርናው ዘርፍ ትኩረት በመስጠት የፋይናንስ ተደራሽነትንና ተጠቃሚነትን ለማስፋት የተለያዩ እርምጃዎችን በፖሊሲ እና እስትራቴጂ ደረጃ እየወሰደ ይገኛል ብለዋል፡፡

የግብርና ፋይናንስ ተጠቃሚነት አሁን ካለበት ደረጃ ከፍ ለማድረግ ተቋማቸው የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ እና ዘርፉን ከሚደግፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራትም ያለውን ቁርጠኝነትን ገልፀዋል፡፡


 

የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሴ የመድረኩ አላማ በግብርና ፋይናንስ ላይ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን መቀነስ እና ለቀጣይ ስራ የሚያግዙ የመፍትሄ ሃሳቦችን ከባለድርሻ አካላት መሰብሰብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ በግብርና ፋይናንስ አገልግሎት ላይ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶች፣ የመፍትሄ ሃሳቦች፣ መልካም ዕድሎች እና በዘርፉ የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ መነሻ ሰነዶች ቀርበው ውይይት እንደተደረገባቸው የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም