ኢትዮጵያ በቻይና አፍሪካ የትብብር ማዕቀፍ ፎረም የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ተሳተፈች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በቻይና አፍሪካ የትብብር ማዕቀፍ ፎረም የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ተሳተፈች
አዲስ አበባ ሰኔ 12/2015(ኢዜአ):- ኢትዮጵያ በቻይና ቤጂንግ በተካሄደው ስምንተኛው የቻይና አፍሪካ የትብብር ማዕቀፍ ፎረም የሚኒስትሮች ጉባኤ እና የቱሪዝም የድርጊት መርሐ-ግብር አስመልክቶ በተደረገው ውይይት ላይ ተሳትፋለች።
በጉባኤው ላይ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር ዳዋኖ ከድር እና ሌሎች የኤምባሲው ተወካዮች ተገኝተዋል።
በሚኒስትሮች ጉባኤው በቻይና እና አፍሪካ ትብብር በተለያዩ መስኮች እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ያሉበት ደረጃ የተገመገመ ሲሆን ትስስሩን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል።
ከጉባኤው ጎን ለጎን በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በ ‘አፍሪካ ቱሪዝም ፕሮሞሽን ኮንፍረንስ’ በጋራ ባዘጋጁት መድረክ ላይ የ ‘ዳካር 2022-24’ የቱሪዝም የድርጊት መርሐ-ግብር ላይ ውይይት ተደርጓል።