የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱኳን ሚደቅሳ የዳግም ህዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን ተመለከቱ - ኢዜአ አማርኛ
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱኳን ሚደቅሳ የዳግም ህዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን ተመለከቱ
ሶዶ ሰኔ 12/2015 (ኢዜአ)፦ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱኳን ሚደቅሳ በወላይታ ዞን ዳግም እየተካሄደ የሚገኘውን ህዝበ ውሳኔ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ጎበኙ።
በዞኑ የሶዶ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በከተማ አስተዳደሩ 187 የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን በነዚህ ጣቢያዎች 935 ምርጫ አስፈፃሚዎች እንደሚገኙ ተመላክቷል።
በወላይታ ዞን የሚካሄደው የዳግም ህዝበ ውሳኔ የድምጽ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ሰላማዊ በሆነ መንገድ እየተካሄደ ነው።