ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ጎበኙ

አዲስ አበባ ሰኔ 10/ 2015 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ አብራሪዎች እና ሰራተኞች የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ጎበኙ።

በጉብኝቱ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰውን ጨምሮ የኢትዮጵያ አየር ሃይልና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በዕለቱ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ከለውጡ ወዲህ እያከናወነ የሚገኘውን የሪፎርም ስራዎች ተጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ አየር ሃይል ብቃት ያላቸውን የሰው ሃብት በመገንባት ላይ መሆኑንም በጉብኝት ላይ ተጠቁሟል።

ለአየር ሃይሉ ምቹ የስራ ከባቢን ከመፍጠር አንጻርም ውጤታማ ስራዎች መስራታቸውንና አየር ሃይሉ ለታላቅ አገር ታላቅ ተቋምን የመገንባት ዓላማ አንግቦ እየሰራ መሆኑም በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም