የመንግስታት ግንኙነት የጋራ የምክክር መድረክ የፊታችን ሰኞ በአዲስ አበባ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
የመንግስታት ግንኙነት የጋራ የምክክር መድረክ የፊታችን ሰኞ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ)፦ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዘጋጅነት የመንግስታት ግንኙነት የጋራ የምክክር መድረክ ከነገ በስቲያ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለጸ።
የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተረፈ በዳዳ የኢትዮጵያ የመንግስታት ግንኙነት ስርዓትን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1231/2013 መሰረት ከተቋቋሙት የመንግስታት ግንኙነት መድረኮች አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።
በጋራ የምክክር መድረኩ በተለያዩ ምሁራን "የመንግስታት ግንኙነት ለጠንካራ ፌዴራል ስርዓት ግንባታ ያለው ሚና" እና "የመንግስታት ግንኙነት ተሞክሮ በኢትዮጵያ እና ቀጣይ አቅጣጫ" በሚሉ ርዕሶች ጽሁፎች ቀርበው ምክክር እንደሚደረግባቸው አመልክተዋል።
በምክክር መድረኩ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የክልል አፈ-ጉባዔዎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች እንደሚሳተፉና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ እንደሚመክሩ ተናግረዋል።