የኢትዮ-ተርኪዬ የንግድ ፎረም በሳምሱን ከተማ ተካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮ-ተርኪዬ የንግድ ፎረም በሳምሱን ከተማ ተካሄደ
አዲስ አበባ ሰኔ 09/2015(ኢዜአ)፡- የኢትዮ ተርኪዬ የንግድ ፎረም በጠረፍ ከተማዋ ሳምሱን ተካሄዷል።
በፎረሙ ላይ በተርኪዬ የኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሐመድ፣የኢትዮጵያ ኢንቨስትመት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን፣የሳምሱን ከተማ ከንቲባ ሙስጠፋ ዴሚር እና ከ70 በላይ የቱርክ ባለሀብቶች ተሳትፈዋል።
ፎረሙ በኢትዮጵያ እና ተርኪዬ መካከል ያለውን የንግድ እና ኢንቨስመንት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚያግዝ አምባሳደር አደም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያን ሰፊ የንግድ እና ኢንቨስትመንት እድሎች እንዳላትም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን በኢትዮጵያ ያሉ የተለያዩ የኢንቨስትመንት እድሎች፣ የፖሊሲ ማሻሻያዎች እና የማበረታቻ ማዕቀፎችን አስመልክቶም ማብራሪያ ሰጥተዋል።