ቀጥታ፡

ጃፓን በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎች ለትምህርት ቤቶች መልሶ ግንባታና ሳኒቴሽን ፕሮግራም የሚውል 8 ነጥብ 1 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አደረገች


አዲስ አበባ ሰኔ 9/2015 (ኢዜአ)፦ ጃፓን በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ለትምህርት ቤቶች መልሶ ግንባታና ሳኒቴሽን ፕሮግራም የሚውል 8 ነጥብ 1 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አደረገች።

የድጋፍ ስምምነቱን በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ እና የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ( ዩኒሴፍ) የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር አቡበከር ካምፖ ጋር ተፈራርመዋል።

ድጋፉ  የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜኑ ግጭት የወደሙ የትምህርት ተቋማት መልሶ ለመገንባት እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ያለመ ሲሆን፤ መሰረታዊ የሆኑ ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ትምህርት ቤቶችን ያሉ ልማቶችን እና የሳኒቴሽን እና ሃይጂን ፕሮግራምን ለመደገፍ ያግዛል ተብሏል።


በዚህም 12 ሺህ ተማሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ የሳኒቴሽን እና ሃይጂን ፕሮግራም ደግሞ 47 ሺህ የሚሆኑ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡


ድጋፉ በኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት እንደሚረዳም ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም