ቀጥታ፡

6ኛው የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ዓመታዊ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ሰኔ 8/2015(ኢዜአ)፡- 6ኛው የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ዓመታዊ ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ብሩክ ታዬን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የቀጣናው የፋይናንስ ዘርፍ አቅም፣ ቀጣናዊ ትስስር፤ የፋይናንስ አቅርቦትና ተደራሽነት፣ የፋይናንስ ዘርፍ ውጤቶች አፈጻጸም፣ ልምዶች፣ የዘርፉ እድሎች እና ተግዳሮቶች ውይይት እንደሚደረግባቸው ተገልጿል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉባኤ የመድን፣ የማይክሮ ፋይናንስ፣ የባንክ እና ሌሎች የፋይናንስ ዘርፍ ተቋማት ተወካዮችና ዓለም አቀፍ የሒሳብ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም