ቀጥታ፡

ቋሚ ኮሚቴው የ2013/14 በጀት ዓመት የጤና መድህን ተደራሽነት እና የገቢ አሳባሰብ አፈጻጸም የኦዲት ግኝቶችን እየገመገመ ነው

አዲስ አበባ ሰኔ 7/2015 (ኢዜአ):- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2013/14 በጀት ዓመት የጤና መድህን ተደራሽነት እና የገቢ አሳባሰብ አፈጻጸም የኦዲት ግኝቶችን በመገምገም ላይ ይገኛል።

በግምገማው ላይ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር መሰረት ዳምጤ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት አመራሮችና እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኦዲት ግኝቶቹን አስመልክቶ ያሉትን ጥያቄዎች በንባብ አቅርቧል።

የኦዲት ግኝቶቹ በርካታ ጉድለቶችን እንዳመላከቱ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ክርስቲያን ታደለ ገልጸዋል።

የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት የስራ ኃላፊዎች ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም