ቀጥታ፡

1 ሺህ 200 አባወራዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ ሰኔ 5/2015(ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዳውሮና ኮንታ ዞኖች ስር የሚገኙ የአባ ቦንጋ እና የጫካ ቦቻ ቀበሌዎች የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን የኢሌክተሪክ አገልግሎት አስታወቀ።

አካባቢዎቹን በኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽ ለማድረግ 19 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉም ተመላክቷል።

ግንባታውን ሰርቶ ለማጠናቀቅ 11 ወራት የፈጀ ሲሆን 7 ኪሎ ሜትር መካከለኛ እና 19 ኪሎ ሜትር ዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ እንዲሁም 5 የተለያዩ አቅም ያላቸው ትራንስፎርመሮች መተከላቸውን ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

አገልግሎቱ ኤሌክትሪክ ያላገኙ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ ሲሆን የአባ ቦንጋ እና የጫካ ቦቻ ቀበሌዎች የበጀት ዓመቱ ዕቅድ አካል መሆናቸውን አስታውቋል፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም