ሀገራዊ ምክክሩ በህዝቦች መካከል መተማመን እንዲኖር ያስችላል - አምባሳደር መሐሙድ ድሪር - ኢዜአ አማርኛ
ሀገራዊ ምክክሩ በህዝቦች መካከል መተማመን እንዲኖር ያስችላል - አምባሳደር መሐሙድ ድሪር
ሐረር ሰኔ 05/2015 (ኢዜአ):- ሀገራዊ ምክክሩ በህዝቦች መካከል መተማመን እንዲኖር ያስችላል ሲሉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሐሙድ ድሪር ገለጹ።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአገራዊ የምክክር ሂደት ላይ አጀንዳ ለማሰባሰብ ስለሚከናወኑ ተግባራትና የውይይት ተሳታፊዎች መረጣ ላይ ከሀረሪ ክልል ነዋሪዎች ጋር በሀረር ከተማ እየመከረ ነው ።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሀሙድ ድሪር በመርሃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት አገራዊ ምክክሩ በህዝቦች መካከል እንዲሁም በዜጎች እና መንግስት መካከል መተማመን እንዲኖር ያስችላል።
በዜጎች መካከል ግጭትን በውይይት በመፍታት ማህበራዊ ውልን ለማደስም ምክክር ሚናው የጎላ መሆኑን አመላክተዋል።
ምክክሩ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ልዩነቶችን ለመፍታት የሚያስችል መሆኑንም አመልክተዋል።
ኮሚሽኑ ባዘጋጀው ውይይት ላይ በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሣተፉ ይገኛል።