የኢትዮጵያ መልሶ ማቋቋም እና መገንባት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ መልሶ ማቋቋም እና መገንባት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ሰኔ 5/2015 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ መልሶ ማቋቋም እና መገንባት የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው ።
በምክክር መድረኩ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፣ ሚኒስትሮች፣ በኢትዮጵያ የአገራት አምባሳደሮች፣ የልማት አጋሮች፣ የተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና ተወካዮች ተገኝተዋል።
የምክክር መድረኩ ዓላማም በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተካሔደው ጦርነት ሳቢያ የደረሰውን ጉዳትና መልሶ ማቋቋም የፍላጎት የዳሰሳ ጥናት ላይ ምክክር በማድረግ ሰው ተኮር ልማት ለማጠናከርና ማህበራዊ ግንኙነትን ለማደስ እንደሆነ ተገልጿል።
የደረሰውን ጉዳትና መልሶ ማቋቋም ፍላጎት ዳሰሳ የጥናት በሸፈናቸው ክልሎች አጠቃላይ 22 ነጥብ 69 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ውድመት መድረሱን ነው የተጠቆመው ።
በማህበራዊ፣ በምርት፣ በመሰረተ ልማት፣ እና ባለብዙ ዘርፎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጾ፤ ለመልሶ ግንባታና ማቋቋም ጥረት እንደሚያስፈልግ ነው የተጠቆመው።
የኢትዮጵያ መንግስት በዓለም ባንክ እና የልማት አጋሮች የቴክኒክ ድጋፍ በመታገዝ ግጭቱ ያደረሰውን ውድመትና ጥፋት እንዲሁም የፈጠረውን ፍላጎት አካታች መረጃ ለመስጠት የጉዳት ፍላጎት ግምገማ ማድረኩም መካሄዱ ተመላክቷል።