ቀጥታ፡

መቻል ደረጃውን ያሻሻለበትን ድል አስመዘገበ

አዲስ አበባ ሰኔ 4/2015(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ28ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር መቻል ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 0 ደረጃውን ያሻሻለበትን ድል አስመዘገበ።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ምንይሉ ወንድሙ በ43ኛው እንዲሁም ግሩም ሐጎስ በ64ኛው ደቂቃ ለመቻል የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ውጤቱን ተከትሎ መቻል በ37 ነጥብ ከነበረበት 12ኛ ደረጃ ወደ 9ኛ ከፍ ብሏል።

በአንጻሩ ወልቂጤ ከተማ በ33 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ28ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ በፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ መድን መካከል ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይደረጋል።

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም