የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን 75 ትራክተሮች ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ ወደ አገር ውስጥ አስገባ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን 75 ትራክተሮች ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ ወደ አገር ውስጥ አስገባ
ኮርፖሬሽኑ በበጀት ዓመቱ ለአርሶ አደሩ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ከሚያስመጣቸው 115 ትራክተሮች ውስጥ ነው 75ቱ ያስገባው።
ቀሪዎቹ ትራክተሮች በቀጣይ ጊዜያት እንደሚገቡ ተጠቅሷል።
ትራክተሮቹ የተገዙበት ኩባንያም በትራክተሮቹ አጠቃቀምና ጥገና ዙሪያ ለኮርፖሬሽኑ ባለሙያዎች የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና እንደሚሰጥም ተገልጿል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክፍሌ ወልደማርያም ትራክተሩ ለኢትዮጵያ መልክዓ ምድር አቀማመጥና የአየር ንብረት ተስማሚ መሆኑን ጠቁመዋል።
የኮርፖሬሽኑን ባለሙያዎችን በተቋሙ ከማሰልጠን ባለፈ ትራክተሩን በአገር ውስጥ የመገጣጠም ውጥን መያዙን ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከእርሻ መሳሪያዎች አቅርቦት በተጨማሪ ከመሬት ዝግጅት እስከ ጎተራ የሚዘልቅ የተቀናጀ የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት እንደሚሰጥ ይታወቃል።