797 የክላሽንኮቭ ጥይት በረቀቀ ዘዴ ደብቆ በህዝብ ማመላለሻ ሲያጓጉዝ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ- የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ - ኢዜአ አማርኛ
797 የክላሽንኮቭ ጥይት በረቀቀ ዘዴ ደብቆ በህዝብ ማመላለሻ ሲያጓጉዝ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ- የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ
አዲስ አበባ ሰኔ 1/2015(ኢዜአ)፦797 የክላሽንኮቭ ጥይት በረቀቀ ዘዴ በጠረጴዛ ስር ደብቆ በሕዝብ ማመላለሻ ሲያጓጉዝ የነበረ ተጠርጣሪ ግለሰብ በአዲስ አበባ ከተማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አሰታወቀ።
መነሻውን ደብረ ብርሃን አድርጎ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሲጓጓዝ የነበረ 797 የክላሽንኮቭ ጥይት ፀረ-ሰላም ኃይሎች እጅ ሳይገባ ፖሊስ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ መያዙን ገልጿል።
ምንም ያህል የወንጀል አፈፃፀም ዘዴው እየረቀቀ ቢመጣም ፖሊስ ራሱን ከጊዜው ጋር እያዘመነ በመምጣቱ ረቂቅ የወንጀል አሠራሮችን መቆጣጠር እንደሚችል ይህ ማሳያ እንደሆነ ተገልጿል።
ሕብረተሰቡም ወንጀል በአገር ኢኮኖሚ እና በሕዝብ ደህንነት ላይ የሚያደርሰውን ከፍተኛ ጉዳት ተገንዝቦ ከፖሊስ ጎን በመሆንና ፖሊስ እያደረገ ያለውን ከፍተኛ ጥረት በማገዝ የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።