ከፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ - ኢዜአ አማርኛ
ከፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ
የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በተለያዩ ጊዜያት የአዲስ አበባ ከተማን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ሲያካሄድ ቆይቷል።
የጋራ ግብረ ኃይሉ ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ ግብረ ኃይሉ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍጠር የተዘጋጁ ኃይሎች እንዳሉ ደርሼባቸዋለሁ ብሏል።
ይህንን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ ተከታታይ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ስለሚያካሄድ ህብረተሰቡ ይህን አውቆ ትብብር እንዲያደርግ፤ በአካባቢው ላይ ፀጉረ ልውጦችን ሲመለከት ጥቆማ እንዲሰጥ እና አካባቢውን እንዲጠብቅ የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ አሳስቧል።
ህብረተሰቡ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙት በ987፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች እንዲሁም በስልክ ቁጥር +251 111 11 01 11፣ +251 115 52 63 03፣ +251 115 52 40 77፣ +251 115 54 36 78 እና +251 115 54 36 81፣ +251 115 54 36 84፣ +251 115 54 38 04፣ +251 115 31 22 08፣ +251 115 31 22 23፣ +251 115 31 22 47፣ +251 115 31 22 20፣ +251 115 31 20 63፣ +251 115 31 20 33፣ +251 115 31 21 31፣ +251 115 31 22 21፣ +251 115 31 20 42፣ +251 115 31 20 05 ጥቆማዎችን በፍጥነት በመስጠት ወይም በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች መረጃውን በአካል በማድረስ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የጋራ ግብረ ኃይሉ ጥሪውን ያቀርባል።
በመጨረሻም የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ በቀጣይ የሚደርስበትን ውጤት ለህዝብ እየገለፀ እንደሚሄድ ያስታውቃል።
የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል
ግንቦት 30 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ