14ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) የመሪዎች ጉባኤ የፊታችን ሰኞ በጅቡቲ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
14ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) የመሪዎች ጉባኤ የፊታችን ሰኞ በጅቡቲ ይካሄዳል
አዲስ አበባ ግንቦት 30/2015(ኢዜአ):- 14ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) የመሪዎች ጉባኤ ሰኞ ሰኔ 5/2015 ዓ.ም በጅቡቲ እንደሚካሄድ ድርጅቱ አስታወቀ።
በስብስባው ላይ የአገራት መሪዎች እና ባለስልጣናት እንደሚሳተፉ ድርጅቱ ባወጣው መረጃ አመልክቷል።
የ13ኛው የኢጋድ የመሪዎች ጉባኤ ሕዳር 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ መካሄዱ የሚታወስ ነው።
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) እ.አ.አ በ1996 የተመሰረተ ቀጣናዊ ተቋም ሲሆን ኢትዮጵያን ጨምሮ ስምንት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን በአባልነት ያቀፈ ድርጅት ነው።
ኢጋድ ቀጣናዊ ትብብር እና ትስስር ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ድርጅት ሲሆን አባል አገራቱ ሰላም እና ደህንነታቸውን እንዲያረጋግጡ እንዲሁም ብልጽግናን እንዲያሳኩ ድጋፍ ያደርጋል።