የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ ሁለት አዳዲስ አባላትን አካተተ - ኢዜአ አማርኛ
የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ ሁለት አዳዲስ አባላትን አካተተ

አዲስ አበባ ግንቦት 28/2015(ኢዜአ)፦የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ ሁለት አዳዲስ አባላትን በኮሚቴው ውስጥ ማካተቱን ገለጸ።
በተለያዩ ምክንያቶች በተጓደሉ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አባላት ምትክ አዳዲሶቹ አመራሮች በብልፅግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ መመረጣቸው ተገልጿል።
በዚህም መሰረት ዶክተር አብዱ ሁሴን እና አቶ ይርጋ ሲሳይ ኮሚቴውን በአባልነት መቀላቀላቸውን ፓርቲው ማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
አመራሮቹ የረጅም አመት የፖለቲካ ልምድ ያካበቱ እና ፓርቲው የጀመረውን ሀገራዊና አካታች የብልፅግና ጉዞ እንደሚያግዙ ታምኖበታል ሲልም አስታውቋል።