ፅንፈኝነትንና አክራሪነትን በመከላከል ጠብቀን እና ተንከባክበን ያቆየነውን አንድነት እና ሰላምን ማጽናት ይገባናል- አቶ አብዱጀባር መሀመድ - ኢዜአ አማርኛ
ፅንፈኝነትንና አክራሪነትን በመከላከል ጠብቀን እና ተንከባክበን ያቆየነውን አንድነት እና ሰላምን ማጽናት ይገባናል- አቶ አብዱጀባር መሀመድ
አዲስ አበባ ግንቦት 28/2015(ኢዜአ)፦ ፅንፈኝነትንና አክራሪነትን በመከላከል ጠብቀን እና ተንከባክበን ያቆየነውን አንድነት እና ሠላማችንን ማጽናት ይገባናል ሲሉ በብልፅግና ፓርቲ ሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ ተናገሩ።
የሀረሪ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ በክልላዊና ሀገራዊ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል።
መድረኩ በክልሉ ሰላምን ለማጠናከር እና ለዘላቂ ልማትና ብልጽግና ለማረጋገጥ በጋራ መቆም እንደሚያስችል ገልጸዋል።
ፅንፈኝነትንና አክራሪነትን በመከላከል ጠብቀን እና ተንከባክበን ያቆየነውን አንድነት እና ሠላማችንን ማጽናት እንደሚገባ ጠቁመው በዚህም አመራሩ የመሪነት ሚናውን በአግባብ እንዲወጣ አሳስበዋል።
መላው የክልሉ ህዝብም እየታየ የሚገኘውን አንፃራዊ ሰላም እና አብሮነትን መጠበቅና መንከባከብ እንዳለበት አመላክተዋል።
ከከፍተኛ አመራሮች በተጨማሪ በክልሉ ከሁሉም ቀበሌዎች የተውጣጡ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይቶች እየተካሄዱ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
ውይይቱ ለሶስት ቀናት እንደሚቆይ ከክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።