ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከብራዚሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር እንደሚወያዩ ገለጹ

239

አዲስ አበባ ግንቦት 28/2015(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከብራዚሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማውሮ ቪዬራ ጋር በኢትዮጵያ እና በብራዚል መካከል ግንኙነትን ስለማጠናከር እና በብዝኃ ወገን ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ከብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማውሮ ቪዬራ ጋር ዛሬ ተገናኝተናል” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመልዕክታቸው “በኢትዮጵያ እና በብራዚል መካከል ግንኙነትን ስለማጠናከር እና በብዝኃ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት እናደርጋለን” ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም