ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በስዊድን ስቶክሆልም ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች አሸንፈዋል - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በስዊድን ስቶክሆልም ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች አሸንፈዋል
አዲስ አበባ ግንቦት 28/2015(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በስዊድን ስቶክሆልም ማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ በበላይነት ጨርሰዋል።
በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ አገራት የአትሌቲክስ ውድድሮች ተካሄደዋል።
በሳምንቱ ከተደረጉ ውድድሮች መካከል በስዊድን የተካሄደው የስቶኮልም ማራቶን ይገኝበታል።
በዚህ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
በወንዶች አትሌት አሸናፊ ሞገስ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ አትሌት ደራራ ሁሬሳ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ጸጋዬ መኮንን ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
በሴቶቹ ውድድር አትሌት ሲፋን መላኩ አሸንፋለች።
አትሌት ሶሮሜ ነጋሽ ሁለተኛ ሆና ስትጭርስ አትሌት የኔነሽ ዲንቄሳ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
በስፔን አልባሴቴ የግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች አትሌት ካሳነሽ ባዜ አሸናፊ ሆናለች።
በደቡብ አፍሪካ በተደረገው የኔልሰን ማንዴላ ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት በቀለች ወሬዮ ሶስተኛ ወጥታለች።
አትሌት ሰላም ገብሬና ትዕግስት አያሌው በቅደም ተከተል አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃን ይዘው ጨርሰዋል።