ከተማዋ ከብክለት የጸዳች ውብና ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ ሁሉም የሚያበረክተውን አዎንታዊ አስተዋጽኦ አጠናክሮ መቀጠል አለበት - ዶክተር ጀማሉ ጀንበሩ

አዲስ አበባ ግንቦት 25/2015 (ኢዜአ) አዲስ አበባ ከተማ ከብክለት የጸዳች ውብና ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ ሁሉም የሚያበረክተውን አዎንታዊ አስተዋጽዖ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ።

 የዘንድሮው የአለም አካባቢ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ50ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ30ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው።

 የአካባቢን ጥበቃ ቀንን አስመልክቶ ከግንቦት 25 እስከ ግንቦት 27 የሚቆይ ኢግዚቢሽን ተከፍቷል።

በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማና ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ጀማሉ ጀንበሩ ከተማዋን ምቹ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በተለይም በመዲናዋ ነዋሪዎችና በተቋማት የሚመነጩ ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎች የተቀመጡ የጽዳት ሕጎች አክብረው እንዲወገዱ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከተማዋ  ከብክለት የጸዳች ውብና ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ ሁሉም የሚያበረክተውን አዎንታዊ አስተዋጽዖ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ነው ያሳሰቡት። 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ዲዳ ድሪባ በበኩላቸው በመዲናዋ የአካባቢ ችግሮች እንዲፈቱ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነው።


 

ለዚህም አካባቢያዊ ደንቦችን፣ ደረጃዎችን መመሪያዎችን በማውጣት በማስተዋወቅ እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች በስፋት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። 

ጎን ለጎንም ሕግና ደንብ በሚተላለፉ አካላት ላይ እርምጃ እየተሰራ እየተወሰደ መሆኑን ገልጸዋል። 

 

 

 

 

 

 

 

 

 በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማና ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ጀማሉ ጀንበሩ ገለጹ። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም