ባለፉት ሦስት ዓመታት በንግድ ስራ ፈጠራ ሀሳብ ውድድር አሸናፊ የሆኑ 381 ወጣቶች አስተማማኝ የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል- የስራና ክህሎት ሚኒስቴር

180

አዲስ አበባ ግንቦት 25/2015 (ኢዜአ)፦ ባለፉት ሶስት ዓመታት "በብሩህ ኢትዮጵያ" የንግድ ስራ ፈጠራ ሀሳብ ውድድር አሸናፊ የሆኑ 381 ወጣቶች ዘላቂ የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ገለጹ።

ለዘንድሮ ውድድር አሸናፊዎች ለእያንዳንዳቸው የስራ ማስጀመሪያ 5 ሺህ ዶላር እንደሚሸለሙ ጠቁመዋል። 

ሚኒስትር ዴኤታው 4ኛው "ብሩህ ኢትዮጵያ 2015" ብሔራዊ የንግድ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር  አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ 

ውድድሩ ዘላቂ የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር የሚረዳ ሀሳብ ያላቸው ወጣቶች የሚሳተፉበት መድረክ መሆኑን አቶ ንጉሱ ገልጸዋል።

"ብሩህ ኢትዮጵያ" የንግድ ሃሳብ ውድድር ከዚህ ቀደም በመንግስት ብቻ ሶስት ጊዜ እንዲሁም ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ደግሞ አራት ጊዜ በድምሩ ሰባት ጊዜ መካሄዱን አስታውሰዋል።

ባለፉት ሶስት ዓመታት በ "ብሩህ ኢትዮጵያ" ፕሮግራም 552 የፈጠራ ሀሳብ ባለቤት ወጣቶች የክህሎት ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉን አመልክተዋል፡፡

ከእነዚህ መካከል 167 ምርጥ የንግድ ፈጠራ ሀሳቦች ለውድድር ቀርበው አሸናፊ ለሆኑት ለስራ ማስጀመሪያ የሚሆን የ1 ሚሊዮን 518 ሺህ ዶላር ሽልማት መሰጠቱንን ሚኒስትር ዴኤታው የተናገሩት።

በዚህም ባለፉት ሶስት ዓመታት ብቻ በፈጠራ ሃሳብ ውድድር አሸናፊ ለሆኑ 381 ወጣቶች "አስተማማኝ  እና ቋሚ የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል" ብለዋል።

እንደ አቶ ንጉሱ ገለጻ፤4ኛው "ብሩህ ኢትዮጵያ 2015" ብሔራዊ የንግድ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር በሚቀጥለው ወር ይካሄዳል።

ከተለያዩ ክልሎች የተመረጡ 200 ተወዳዳሪዎች ከግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቡራዩ የተሰጥኦ ማበልጸጊያ ትምህርት ቤት ገብተው የስራ ፈጠራን የተመለከቱ ስልጠናዎ እንደሚወስዱ አመልክተዋል።

ስልጠናውን ከወሰዱት መካከል ለውድድር የሚቀርቡ 70 ባለተሰጥኦዎችን ለመለየት መርሐ-ግብር መዘጋጀቱን አንስተው፤ለ50 አሸናፊዎች ለእያንዳንዳቸው የስራ ማስጀመሪያ 5 ሺህ ዶላር እንደሚሸለሙ ገልጸዋል።

የዘንድሮው ውድድር ክልሎችን በስፋት ተደራሽ አድርጓል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ይህም በሁሉም አካባቢ ያሉ እምቅ የንግድ ፈጠራ ሀሳቦችን አካታች በሆነ መንገድ ማሳተፍን ታሳቢ ያደረገ  መሆኑን ተናግረዋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

መካሔዱን የገለጹት አቶ ንጉሱ 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም